CLOSED

አንደኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ፡ በሸገር ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙት ኮዬ ፈጬ፣ ቡራዩ፣ እና መልካ ኖኖ ከፍለ ከተሞች ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል

SC

Shaggar City Land Office

Government Organization

Location

Oromia

Category

IT & Software

Reference Number

CHR-004061

Tender Type

Open

Description

በሸገር ከተማ አስተዳደር የሸገር ከተማ መሬት ጽ/ቤትየ1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ የሸገር ከተማ መሬት ጽ/ቤት ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁና በቆዬ ፈጬ፣ በቡራዩ፣ እና በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል። የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ቴሌብር (telebirr) በመጠቀም shaggarland.2merkato.com ወይም shaggarland.afrotender.com ድረ-ገጾች ላይ በመግባት በኦንላይን መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሰነድ ግዢውን ከሚያዝያ 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት መፈፀም ይችላሉ፤ ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያሰነድ፣ ሲፒኦ (CPO)፣ የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ ሰነዱን ለመግዛት የከፈሉበትን የቴሌብር ደረሰኝ ወይም ስሊፕ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በፖስታ (በኤንቨሎፕ) በማሸግ እስከ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ንፋስ ስልክ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወይም ጎተራ ማሞ ኮንዶሚኒየም አካባቢ የሸገር ከተማ መሬት ጽ/ቤት በሚገኝበት የሸገር ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት (MESOB) ህንፃ ምድር ቤት (በጉግል ቦታ ማሳያ) https://maps.app.goo.gl/toCJZwKSxr2Sxckv7?g_st= ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 3 የስራ ቀናት መስሪያ ቤቱ ለዚሁ ጨረታ ባዘጋጀው ቦታ ላይ የሚከፈት ሆኖ፣ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃው በማስታወቂያ ይገለፃል። የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሚያዝያ 08/2018 ዓ.ም በወጣው ከለቻ ኦሮሚያ እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሱት ድረ ገጾች መረጃውን ማግኘት ይችላሉ። ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በመሬት ጽ/ቤቱ ስልክ ቁጥር +251-11-47-095-44 ወይም +251-11-47-080-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል። በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፤ 1. ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ) ብር በቴሌብር (Telebirr) በመክፈል shaggarland.2merkato.com ወይም shaggarland.afrotender.com በተባሉት ድረ-ገጾች በመጠቀም የጨረታ ሰነዱን ከሚያዝያ 05 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ድረስ በመግዛት ማውረድ (Download ማድረግ) ትችላላችሁ። 2. ማንኛውም በዚህ የሊዝ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በቁጥር አንድ ላይ በተጠቀሰው ድረ-ገጽ ሰነዱን ለመግዛት በመጀመሪያ በራሱ ስም ብቻ ከራሱ ሂሳብ ላይ ቀንሶ መግዛት አለበት። 3. ተጫራቾች መሬቱ ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ የቦታውን ሁኔታ ካየ በኋላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 4, አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መወዳደር አይችልም። ከአንድ ቦታ በላይ ተወዳድሮ ከተገኘ ከጨረታው ውጭ ይሆናል። 5. ተጫራቾች ሞልተው የሚያቀርቡት የጨረታ መልስ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ (Bidders Manual) ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያሟላ መሆን አለበት። 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የቦታውን ስፋት በመነሻ ዋጋ በማባዛት ከሚመጣው ጠቅላላ ዋጋ 5% ያነሰ መሆን የለበትም። ይህ የ

Source

Source Link Available for Members

Sign up free to access the original tender posting and full details

Important Dates

Published

August 5, 2026

Closing Date

April 30, 2026

Closed 97 days ago

Contact Information

Organization

████████████████

Phone

+251 ██ ███ ████

Email

████@████.gov.et

Login to view

Share This Tender