BIDDING OPEN

አርቲክራፍት ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህ ቱቦላሬ ብረት (RHS Metal Steel) 50mmx50mm, thickness 2-2.5mm (Mix) and 2.4m length የሆነውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ባለበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል

አኢ

አርቲክራፍት ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህ

Government Organization

Location

Addis Ababa

Category

Construction

Reference Number

CHR-008982

Tender Type

Open

Description

ቀን፡ መስከም 5/2019 ዓ.ም የጨረታ መለያ ቁጥር፡ Arti/RHS/001/2019የጨረታ ማስታወቂያ ድርጅታችን አርቲክራፍት ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህ ከዚህ በታች የተገለጸውን ቱቦላሬ ብረት (RHS Metal steel) 50mmx50mm, thickness 2-2.5mm (Mix) and 2.4m length የሆነውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ባለበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች እቃዉን ባለበት ቦታ በማየት የምትገዙበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በመግለፅ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን 5/1/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 10/1/2019 ዓ/ም ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የስራ ቀናት የድርጀቱ ሽያጭ ክፍል ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ጨረታው መስከረም 11/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ይከፈታል። ማሳሰቢያ፡ 1.የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ፡ ተጫራቾች ዋጋቸውን ማቅረብ የሚችሉት ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዞ በተዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ብቻ መሆን አለበት። 2.የታክስ ሁኔታ፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የነጠላም ሆነ የአጠቃላይ ዋጋ 15% ቫትን (15% VAT) ያካተተ መሆን አለበት። 3.የዘገዩ ጨረታዎች፡ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት (መስከረም 11/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት) በኋላ የሚመጡ ጨረታዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። በተጨማሪም ተጫራች ያስገባውን ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡ 4.የክፍያ እና ዕቃ ማንሻ ጊዜ፡ የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ አለበት፤ እንዲሁም ክፍያ ከፈጸመበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን አንስቶ ማጠናቀቅ ይኖርበታል። 5.የጨረታ ማስከበሪያ (CPO): ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩበት ወቅት በድርጅታችን ‘’Articraft industry PLC ስም (በኢትዮጵያ ንግደ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000347206273) የተዘጋጀ CPO 5,000 (አምስት ሺህ) ብር ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል። ለአሸናፊው ከጠቅላላ ሂሳቡ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለሳል። 6.እቃው ከተሽጠ በኋላ ያለው ሃላፊነት፡ የቱቦላሬ ብረት (RHS) ጨረታው አሸናፊ ከድርጅታችን ገዝቶ ከወሰደ በኋላ ያለውን ማንኛውንም በመንግስት የሚጠየቁ ክፍያዎችን ካሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል፡፡ 7.ሕጋዊ ሰነዶች: ተወዳዳሪዎች ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው። አሸናፊው ተጫራች ውል ሲፈራረም ኦሪጂናል ንግድ ፈቃዱን ማሳየት ይኖርበታል። 8.መብት: ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ : አድራሻ፡- አርቲክራፍት ኢንደስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህ ዱከም /መንደሎ/ ባጃጅ መገጣጣሚያ ፊት ለፊት

Source

Source Link Available for Members

Sign up free to access the original tender posting and full details

Important Dates

Published

September 16, 2026

Closing Date

September 21, 2026

4 days remaining

Contact Information

Organization

████████████████

Phone

+251 ██ ███ ████

Email

████@████.gov.et

Login to view

Share This Tender