BIDDING OPEN

ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የፕላስቲክና የብረት በርሜሎችና ጀሪካኖች፣ አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ ቆርቆሮ፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት፣ የእንጨት ፓሌቶች፣ ማዳበሪያና ላስቲክ፣ ካርቶን፣ የተለያዩ የማሽን አካላት፣ አሮጌ የእሳት ማጥፊያዎች እንዲሁም ሌሎችንም ጨምሮ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

EL

Ethio Leather Industry

Government Organization

Location

Addis Ababa

Category

Construction

Reference Number

CHR-008840

Tender Type

Open

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የፕላስቲክና የብረት በርሜሎችና ጀሪካኖች፣ አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ ቆርቆሮ፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት፣ የእንጨት ፓሌቶች፣ ማዳበሪያና ላስቲክ፣ ካርቶን፣ የተለያዩ የማሽን አካላት፣ አሮጌ የእሳት ማጥፊያዎች እንዲሁም ሌሎችንም ጨምሮ ባለበት ሁኔታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በድርጅቶቻችን አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ፣ አቢሲኒያ ቆዳ ፋብሪካ ዩኒቨርሳል የቆዳ ውጤቶችና ጥቁርአባይ ጫማ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ የፕላስቲክና የብረት በርሜሎችና ጀሪካኖች፣ካርቶን፣ላስቲክና ማዳበሪያ፣ጎማዎች ያገለገለ ቆርቆሮዎች፣ ቁርጥራጭ ብረታብረቶችና ሌሎችም ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሠነድ ሳሪስ በሚገኘው አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ (ፎንታኒና ጫማ) ሽያጭ ክፍል የማይመለስ ብር 115 (አንድ መቶ አስራ አምስት ብር) በመክፈል ከ ሀሙስ 28/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ 04/01/2019 ዓ.ም ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ ጠዋት 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከከሰዓት 7፡00 እስከ 11፡00 መውሰድ ይቻላል፡፡ 2. ልዩ ልዩ ዕቃዎች ከ 28/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ 04/01/2019 ዓ.ም አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ ፣አቢሲኒያ ቆዳ ፋብሪካ፣ ዩኒቨርሳል የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም ጥቁር አባይ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት በሥራ ሰዓት ብቻ በአካል በመገኘት ዕቃዎችን ማየት ይቻላል፡፡ 3. ተጫራቶች ለሚጫረቱበት ዕቃ ለጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (አምሣ ሺህ) CPO (ETHIO LEATHER INDUSTRY PLC) በሚል ስም ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 4. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው CPO አሸናፊ ለሆኑት ያሸነፉበትን ዕቃ ጨርሰው ሲያነሱ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ተሸናፊ ለሆኑትም ያስያዙት CPO የጨረታ ውጤት ተገልጾ በቃለ ጉባኤ ከፀደቀ በኋላ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ 5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ቀን 04/01/2019 ዓ.ም ከስዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡ 6. ተጫራቶች ያስገቡት የጨረታ ሰነድ 04/01/2019 ዓ.ም ከስዓት በኋላ 8፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ሳሪስ በሚገኘው አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ (ፎንታኒና ጫማ) ሽያጭ ክፍል በግልጽ ይከፈታል፡፡ 7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ማሳሰቢያ !!! የበርሜል፣ የጀሪካን፣ ላስቲክ እና ማዳበሪያ ተጫራጮች ጨረታውን ለመሳተፍ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የሰጠውን ፍቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል አድራሻ ሳሪስ በሚገኘው አዋሽ ቆዳ ፋብሪካ ስልክ ቁጥር 0114 71 75 85

Source

Source Link Available for Members

Sign up free to access the original tender posting and full details

Important Dates

Published

September 3, 2026

Closing Date

September 14, 2026

10 days remaining

Contact Information

Organization

████████████████

Phone

+251 ██ ███ ████

Email

████@████.gov.et

Login to view

Share This Tender