BIDDING OPEN

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በሪጅኑ ስር የተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉትን የብራንዲንግ ስራዎችን በማስታወቂያ እና ህትመት ስራ ዘርፍ የተሰማሩትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

ET

Ethio Telecom

Government Organization

Location

Addis Ababa

Category

Printing

Reference Number

CHR-009274

Tender Type

Open

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በሪጅኑ ስር የተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉትን የብራንዲንግ ስራዎችን በማስታወቂያ እና ህትመት ስራ ዘርፍ የተሰማሩትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። RFQ No. 4287355 በዚሁ መሰረት በማስታወቂያ እና ህትመት ስራ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሁለት አመት የስራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። መስፈርት፡- 1. ጨረታው ከመስከረም 29 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። 2.ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል። 3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በማስታወቂያ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል። 5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸዉን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው። 6.ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም። 7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል። 8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘገጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል። ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

Source

Source Link Available for Members

Sign up free to access the original tender posting and full details

Important Dates

Published

October 7, 2026

Closing Date

October 27, 2026

19 days remaining

Contact Information

Organization

████████████████

Phone

+251 ██ ███ ████

Email

████@████.gov.et

Login to view

Share This Tender