BIDDING OPEN
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ በሚገኙ የሥራ ቦታዎቹ እንደየፍላጎቱ የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ አስተማማኝ አጋሮችን ይፈልጋል
SE
Safaricom Ethiopia
Government Organization
Location
Addis Ababa
Category
IT & Software
Reference Number
CHR-009366
Tender Type
Open
Description
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ - የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) ጥሪ የተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት አቅራቢዎችን ለማወዳደር የወጣ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ መለያ ቁጥር (EOI Reference): ይፋ የተደረገበት ቀን፡ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 03 ቀን 2019 ዓ.ም. የማመልከቻው መዝጊያ ቀን፡ እስከ ሰኞ፣ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ አዘጋጅ፡ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጨረታ ማስገቢያ የኢሜይል አድራሻ: bids@safaricom.et 1. (AIMS AND OBJECTIVES) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ በሚገኙ የሥራ ቦታዎቹ እንደየፍላጎቱ የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ አስተማማኝ አጋሮችን ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ብቁ የሆኑ የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት አቅራቢዎችን ለመለየት ይህንን የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ (EOI) አውጥቷል። ፍላጎትና አቅም ያላቸው አቅራቢዎች በመላ አገሪቱ ለሚገኙ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሠራተኞች በሚፈለገው መጠን እና በሚደረገው የአገልግሎት ስምምነት (SLA) መሠረት በሁሉም የሥራ ፈረቃዎች የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ ጥሪ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሚጠብቀውን የአገልግሎት ደረጃ በሚያሟላ መልኩ አገልግሎቱን በጥራትና በተሻለ አኳኋን ለማቅረብ የሚያስችል በቂ አቅም ያላቸውን አቅራቢዎች ለመለየት ያለመ ነው 2. የተሳትፎ ፍላጎት ማሳወቂያ መስፈርቶች (EOI REQUIREMENTS) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ፍላጎትና አቅም ያላቸው የተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት አቅራቢዎች ከታች የተዘረዘሩትን መረጃዎችና ሰነዶች በማያያዝ የተሳትፎ ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁ ይጠይቃል፡ አቅራቢው በሁሉም ከተሞችና የሥራ ማስኬጃ ቦታዎች በመላ አገሪቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የተረጋገጠ አቅም እና የሥራ ልምድ ሊኖረው ይገባል። አቅራቢው የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ሊኖረው ይገባል። የድርጅቱ መገለጫ (Company Profile)፣ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ እና የመመሥረቻ ጽሑፍ (Memorandum of Association)። በተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት አቅራቢነት የቆየበት የሥራ ልምድ ዓመታት፤ አነስተኛው መስፈርት ሁለት (2) ዓመት ነው። የድርጅቱን የፋይናንስ አቅም የሚያረጋግጥ የተረጋገጠ የኦዲት ሪፖርት እና/ወይም የባንክ ሂሳብ መግለጫ (Audited Statement of Accounts / Bank Statement)። የተሸከርካሪዎችን እንቅስቃሴ የመከታተልና ወቅታዊ መረጃ የመስጠት ማረጋገጫ — የተከራዩ ተሸከርካሪዎች የሚገኙበትን ቦታ የሚያሳይ መረጃ በሣምንት 7 ቀን፣ በቀን 24 ሰዓት (24/7) የማግኘት ዕድል ማመቻቸት። የጂፒኤስ (GPS) መከታተያ የተገጠመላቸውና ለጉዞ ብቁ የሆኑ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም የተከላካይ አነዳድ (Defensive Driving) ሥልጠና የወሰዱ አሽከርካሪዎችን በማቅረብ የድርጅታችንን የደኅንነት መሥፈርቶች ማሟላት የሚችል 3. በተጫራቾች የሚሞላ የአሠራር ደንብ ማክበሪያ ማረጋገጫ (STATEMENT OF COMPLIANCE) ተወዳዳሪዎች የሚከተለውን የማረጋገጫ ቅጽ ሞልተው በፊርማና ማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡ ተ.ቁ (#) የዝርዝር መግለጫ (Item Description) አሟላለሁ/አላሟላም (Comply Yes/No) አስተያየት (Remarks) ሀ ከመጀመሪያው ግንኙነት ጀምሮ በስምምነቱ (SLA) መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ በየትኛውም ቦታ ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት 24/7 ያለማቋረጥ ለማቅረብ ቁርጠኝነት። ለ በተስማማነው ውልና ሁኔታዎች መሠረት የታሰበውን የተሸከር
Source
Source Link Available for Members
Sign up free to access the original tender posting and full details
Important Dates
Published
October 14, 2026
Closing Date
October 26, 2026
8 days remaining
Contact Information
Organization
████████████████
Phone
+251 ██ ███ ████
████@████.gov.et
Login to view
Similar Tenders
Deutsche Gesellschaft für Internationale Zusammenarbeit (GIZ) GmbH Invites Bids for the Procurement and Installation of Backup Storage Battery, Inverter, with Accessories (Bid Reference Number: 10059625)
GIZ Office Addis Ababa
Closes in 12 days
View Details
Imagine 1day International Organization (I1D) Invites Sealed Bids for the Supply of LCD Projectors, Speakers, and 128 GB Dual-Interface Flash Disks under the Leaders in Teaching Ethiopia (LiTE) Program (Re-Invitation Bid No: I1D/OBP-I1D-042/2026)
Imagine1day International
Closes in 12 days
View Details
UNICEF wishes to invite you to submit a proposal for Establishment of Long Term Agreement for 24+24 months for the provision of Audio-visual Production Service.
UNICEF Ethiopia
Closes in 24 days
View Details