CLOSED
ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት የቲክቶክ ማስተዋወቂያ (Boosting) ስራን በኃላፊነት ወስዶ የሚያከናውን የዲጂታል ሚዲያ ማርኬቲንግ ወይም የማስታወቂያ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል
TE
Tamera Economic Development Organization
Government Organization
Location
Addis Ababa
Category
Printing
Reference Number
CHR-006989
Tender Type
Open
Description
የጨረታ ማስታወቂያ የቲክቶክ ማስተዋወቂያ (Boosting) እና ዲጂታል ተደራሽነት አገልግሎት — ደህንነቷ የተጠበቀ ከተማ (Safe City Project) የጨረታው መረጃ (Tender Document) የፕሮጀክቱ ትኩረት ደህንነታቸው የተጠበቁ ቦታዎች ተነሳሽነት፣ በሴቶችና ሴት ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች (VAWG) መከላከል እና የሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማሳደግ የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ቲክቶክ (TikTok) የወጣበት ቀን ጁን 11/ 2026 ማመልከቻው የሚዘጋበት ቀን ጁን 18/ 2026 1. መግቢያ እና የጀርባ ታሪክ (Introduction & Background) ደህንነቷ የተጠበቀ ከተማ (Safe City Project) ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢን ለመፍጠር፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን (VAWG) ለመከላከል እና ዘላቂ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። በዚሁ ስራ ውስጥ ህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ እና አወንታዊ የባህሪ ለውጥ ለማምጣት በከፍተኛ ጥራት የተዘጋጁ የዲጂታል ቅስቀሳ እና የውሳኔ ሃሳብ (Advocacy) ቪዲዮዎችን አዘጋጅተናል። የእነዚህን ቪዲዮዎች ህዝባዊ ተደራሽነት ከፍ ለማድረግ፣ የማህበረሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ እና በዲጂታል መንገድ ቅስቀሳውን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ቪዲዮዎቹ በቲክቶክ (TikTok) መድረክ ላይ እንዲሰራጩ ታቅዷል። ይህንን እቅድ በብቃት ማሳካት እንዲቻል የቲክቶክ ማስተዋወቂያ (Boosting) ስራን በኃላፊነት ወስዶ የሚያከናውን የዲጂታል ሚዲያ ማርኬቲንግ ወይም የማስታወቂያ ድርጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። 2. የሥራው ዓላማ (Objective of the Assignment) የዚህ ስራ ዋና ዓላማ የቲክቶክ ቪድዮ ማስተዋወቂያ (Boosting) ስትራቴጂን በመንደፍ፣ በተግባር ላይ ማዋል እና የሚለቀቁትን ቪድዮዎች ሂደታቸውን መከታተል ነው፡፡ 3. መስፈርቶች እና የብቃት መመዘኛዎች (Qualifications) ተጫራች ድርጅቶች የሚከተሉትን አነስተኛ መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፦ በቲክቶክ ማስታወቂያ ማስተዳደሪያ (TikTok Ads Manager) ላይ በተግባር የተረጋገጠ የሚከፈልባቸው የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎችን የመምራት የስራ ልምድ ያለው። Ngo ወይም ለትርፍ ባልተቋቋሙ ድርጅቶች ዙሪያ በሚሰሩ ተቋማት ላይ የዲጂታል ቅስቀሳ ስራዎችን ከዚህ ቀደም የሰሩ ቢሆን ይመረጣል። ዘመናዊ የዲጂታል መሳሪያዎችን የመጠቀም ብቃት ያለው። 4. የፕሮፖዛል አቀራረብ እና ማመልከቻ መመሪያ (Submission Guidelines) ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ፕሮፖዛላቸውን ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት በተለያዩ ሰነዶች ማቅረብ አለባቸው፦ ሀ. የቴክኒክ ፕሮፖዛል ይዘት (Technical Proposal Component) የድርጅቱ መገለጫ (Company Profile)፦ የድርጅቱን አጠቃላይ የዲጂታል ማርኬቲንግ አቅም፣ የሰው ኃይል እና መዋቅር የሚያሳይ አጭር መግለጫ። የስራ ልምድ ማረጋገጫ (Case Studies)፦ ከዚህ ቀደም በቲክቶክ ላይ በተሳካ ሁኔታ የተከናወኑ የቪድዮ ማስተዋወቂያ ስራዎች ማሳያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የአሰራር ዘዴ (Methodology)፦ ለዚህ ስራ የሚሆን ስትራቴጂን የሚገልጽ አጭር የአሰራር ዕቅድ። ለ. የፋይናንስ ፕሮፖዛል ይዘት (Financial Proposal Component) የድርጅቱን የአገልግሎት ክፍያ (Agency Management Fee) እና ለቲክቶክ የሚከፈለውን ቀጥተኛ የማስታወቂያ በጀት (Direct Ad Spend/Boosting Budget) በግልጽ ነጣጥሎ የሚያሳይ ዝርዝር ወጪ ማካተት ይጠበቅባቸዋል። አድራሻ
Source
Source Link Available for Members
Sign up free to access the original tender posting and full details
Important Dates
Published
August 5, 2026
Closing Date
June 18, 2026
Closed 48 days ago
Contact Information
Organization
████████████████
Phone
+251 ██ ███ ████
████@████.gov.et
Login to view