CLOSED
ዋን ኤከር ፈንድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው የአርዘሊባኖስ ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
OA
One Acre Fund
Government Organization
Location
Addis Ababa
Category
Agricultural
Reference Number
CHR-008789
Tender Type
Open
Description
ለአርዘሊባኖስ (Arzelibanos (Casuarina equisetifolia)) ዘር ግዢ የወጣ ጨረታ ዋን ኤከር ፈንድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው የአርዘሊባኖስ ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ይህንን ዘር ችግኞችን ለማፍላት ጥቅም ላይ የሚዉል ሲሆን፣ ችግኞችን ለአርሶ አደሮች በማከፋፈል (በማሰራጨት)፣ አርሶ አደሮቹ ዛፎችን በማልማት ሀብታቸውን እንዲጨምሩ፣ ገቢያቸውን እንዲያሰፉ እና አካባቢያቸውን እንዲያለሙ (እንዲያሻሽሉ) ይደረጋል። አጠቃላይ የሚያስፈልገው የዘር መጠን 207,976,844 ዘሮች ሲሆን፣ ይህም በአንድ ኪ.ግ 970,000 ዘሮች እንዳሉ በመገመት ባጠቃላይ 215 ኪ.ግ የአርዘሊባኖስ ዘር ይፈለጋል። ይህ መጠን ዉሉ እስኪፈረም ድረስ ሊቀየር ይችላል። የግዢ ሂደትና ጠባይ (ዘሩ ከመሰብሰቡ በፊት ወይም ከተሰበሰበ በኋላ ከ አቅራቢው ጋር ውሉን እንፈራረማለን) የግዢ ሂደቱ እንደ ዘር መሰብሰቢያ የጊዜ ሰሌዳው ይለያያል። ዋን ኤከር ፈንድ በጨረታው ቀን አስቀድሞ የተሰበሰበ ዘር ሊገዛ ይችላል፣ ወይም ገና ያልተሰበሰበ ዘር ሊገዛ ይችላል። ዘሩ በጨረታው ጊዜ አስቀድሞ ከተሰበሰበ፣ ዋን ኤከር ፈንድ ከተመረጡ አቅራቢዎች ናሙናዎችን ይሰበስባል። እነዚህ ናሙናዎች በጥራት ላይ ተመስርተው ይነፃፀራሉ። የተመረጠው ሻጭ ዘሮችን በሚመለከተው የኳራንቲን ባለስልጣን እንዲመረመር ያደርጋል። ዘሩ ገና ካልተሰበሰበ፣ ዋን ኤከር ፈንድ እናት ዛፎችን እንዲመለከት ባለሙያ ይልካል። ባለሙያው መመሪያ ይሰጣል እንዲሁም ይመለከታል። ናሙናዎች ከሚሰበሰበው ዘር ይወሰዳሉ እና በሚመለከተው የኳራንቲን ባለስልጣን ይፈተሻሉ፡፡ በጨረታው ላይ አስቀድሞ የተሰበሰበ የአርዘሊባኖስ ዘር ከሆነ ቀኑን ይጥቀሱ ወይንም ኮንትራቱ ከተፈረመ በኋላ ዘሩን ለመሰብሰብ እንደሚፈልጉ በጨረታው ላይ ይግለጹ የጥራት ዝርዝር መገለጫዎች፡ ዘሮቹ ከቆሻሻ እና ከሌሎች ባዕድ ነገሮች ንጹህ መሆን አለበት ዘሮቹ ከሚታወቅ የአርዘሊባኖስ የዘር ምንጭ መሰብሰብ አለባቸው። ዘሩ ቀድሞ የተሰበሰበ ከሆነ፣ የተሰበሰበበት ጊዜ ከ 1 አመት በታች መሆን አለበት። ዘሩ ከመሰብሰቡ በፊት ወይም በኋላ ከአሽናፊው አቅራቢ ጋር ውሉን እንፈርማለን። ይህ ውል ዘሩ ሊያሟላቸው የሚገባ ልዩ የጥራት መለኪያዎችን ያካትታል። ዘሩ ከተሰበሰበ በኋላ እነዚያን የጥራት መለኪያዎች ካላሟላ፣ OAF( ዋን ኤከር ፈንድ) የክፍያ መጠኑን ይቀንሳል ወይም ደግሞ ውሉን ሙሉ በሙሉ ሰርዞ ማንኛውንም ቅድመ ክፍያ እንዲመለስ ያደርጋል። እባኮትን የሚከተለውን ቅጽ ሞልተው ፈርመዉ ማህተም በማድረግ ከታች በተቀመጡት በ አንዱ ይላኩ። ኢሜይል ethiopia.bidsubmissions@oneacrefund.org የቴሌግራም @oafbidsubmissions ለበለጠ መረጃ 0985654565 ይደውሉ። ሁሉም ተጫራቾች እስከ መስከረም 8 2019 ዓ.ም ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዘግይተው የሚቀርቡ ጨረታዎች ውድቅ ይሆናሉ፡፡ ጥያቄ መልስ የአንድ ኪሎ ግራም የተጣራ የአርዘሊባኖስ ዘር ዋጋ? ዘሩ የተሰበሰበው ቀን ወይም የሚሰበሰብበት ቀን መቼ ነው? ወሩን ጨምረው ያስገያስገቡ ዋን ኤከር ፈንድ የጥራት ፍተሻ እንዲያካሂድ ዘሩ ተሰብስቦ እና ተጣርቶ እንዳለቀ ወድያዉኑ ታደርሳለህ? የዘር ምንጭ የት ነው? ወይስ የዘሮቹ እናት ዛፎች የሚገኙት የት ነው? (ክልል እና ወረዳ) የዘሩ ጥራት በኮንትራቱ ላይ የተገለጹትን የ ጥራት ደረጃዎች ካላሟላ ሁኔታውን ለማሻሻል እና የጥራት ደረጃዎችን ለማሟላት ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳሉ? 215 ኪሎ ግራም (207,976,844 ዘር) ሙሉ ምርት በስንት ቀን ዉስጥ ማቅረብ ይችላሉ? በአጭር ቀን ዉስጥ ማቅረብ የሚችል
Source
Source Link Available for Members
Sign up free to access the original tender posting and full details
Important Dates
Published
August 29, 2026
Closing Date
September 18, 2026
Closed 29 days ago
Contact Information
Organization
████████████████
Phone
+251 ██ ███ ████
████@████.gov.et
Login to view
Similar Tenders
ABAYS Trading P.L.C. (Almi Products) invites qualified suppliers, manufacturers, farmers' cooperatives and traders to submit sealed bids for the Supply of Raw Materials (Spices, Seeds, Pulses, Flour, Palm Oil, Sugar, Coffee, Salt and Firewood).
ABAYS Trading
Closes in 17 days
View Details
አርቲክራፍት ኢንዱስትሪስ (Articraft Industries) ለነጋዴ ገዢዎች፣ ለንግድ ተቋማት እና ለድርጅቶች የሚሆን የአኩሪያተር ዘይት (Crude Soybean Oil) እና የተጣራ የአኩሪያተር ዘይት (Refined Soybean Oil) ለሽያጭ ማቅረብ ይፈልጋል
ARTICRAFT INDUSTIRIES
Closes in 12 days
View Details