CLOSED
ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ/የተ/ግ/ማህበር (ኖክ) በቃሊቲ መጋዘን ውስጥ የሚገኙትን ባለ 1ኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ ፓሌቶች፣ ኤምዲኤፍ መደርደሪያዎችና ቦርዶች፣ ስብርባሪ እንጨቶች እና የተለያዩ ፕላይዉዶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
NO
National Oil Ethiopia
Government Organization
National Oil Ethiopia has issued a Construction tender in Addis Ababa, Ethiopia. Published 28 Oct 2026. Bidding closed 5 Oct 2026. Reference: CHR-009563.
Location
Addis Ababa
Category
Construction
Reference Number
CHR-009563
Tender Type
Open
Description
ጉዳዩ፡- ጨረታን ይመለከታል፡፡ ኩባንያችን ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን ባለ 1ኛ ደረጃ ፣2ኛ ደረጃ ፓሌቶችን ፣ ኤምዲኤፍ መደርደሪያ (MDF shelf)፣ ኤምዲኤፍ ቦርድ (MDF) sheet፣ ስብርባሪ እንጨቶች እና የተለያዪ ፕላይዉድ (Plywood) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። የእቃው ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል። ተ.ቁ የፓሌት ዓይነት ብዛት 1 1ኛ ደረጃ ፓሌት (ቀይ) 60 2 2ኛ ደረጃ ፓሌት 160 3 ኤምዲኤፍ መደርደሪያ (MDF shelf) 5 4 ኤምዲኤፍ ቦርድ (MDF sheet) ባለበት በጠቅላላ 5 ስብርባሪ እንጨቶች ባለበት በጠቅላላ 6 ፕላይዉድ (Plywood) (1.2m × 2.3m) 1,320 7 ፕላይዉድ (Plywood) (1.1m x 1.1m) 2,400 8 ፕላይዉድ ኮምፐርሳቶ (Plywood) (1.2m × 2.3m × 2mm) 80 9 ፕላይዉድ ፋይዚት (Plywood) 1.2m × 2.3m 310 ስለሆነም ድርጅታችን ከላይ የተዘረዘሩትን የእንጨት ውጤቶች ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል። በተጨማሪም ተጫራቾች ፓሌቶቹን እንደከዚህ ቀደም መምረጥ እንደማይችሉ ከወዲሁ ማሳሰብ ይወዳል። ከላይ ለተጠቀሱት እቃዎች ዋጋ በመስጠት መወዳደር ይቻላል። እቃዎቹን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ጨምሮ ቦታው ላይ በመመልከት የሚገዙበትን ዋጋ ከ15 በመቶ ቫት ጋር በመግለጽ ድርጅቱ ለዚህ ጨረታ ያዘጋጀውን ፎርም በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል። ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ሊሆን ይገባል። እንዲሁም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማቅረብ መጫረት ይቻላል። አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ በተገለጸለት በሦስት የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን በአንድ ጊዜ ክፍያ መፈጸም ይኖርበታል። ይህንን ባይፈጽም ለጨረታው ያስያዘውን ገንዘብ በሙሉ የማይመለስ በመሆኑ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል። አሸናፊ እቃውን በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር) ከቃሊቲ መጋዘን ማንሳት አለበት። ይህ ባይሆን የመጋዘን ኪራይ በቀን 3,000.00 ብር ይከፍላል። ሙሉ ክፍያ ሲፈጽም እና ሙሉ በሙሉ እቃዎቹ ከቃሊቲ መጋዘን ሲነሱ ብቻ ሲፒኦው ተመላሽ ይሆናል። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁ. 011-618-7165 ወይም 011-439-0378 መደወል ይቻላል። አድራሻ፡- ቦሌ ኤርፖርት መንገድ ከፍሬንድሺፕ ህንፃ ፊት ለፊት ያለው የኖክ ዋ/መስሪያ ቤት ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ማህበር (ኖክ)
Source
Source Link Available for Members
Sign up free to access the original tender posting and full details
Important Dates
Published
October 28, 2026
Closing Date
October 5, 2026
Closed 23 days ago
Contact Information
Organization
████████████████
Phone
+251 ██ ███ ████
████@████.gov.et
Login to view
Similar Tenders
HelpAge Ethiopia is now seeking bids from qualified bidders’ grade 7 and above contractors for the construction of Accessible Household Latrines in Sherkole, Tsore, Ura and Bambasi refugee camps, in Benishangul Gumuz, Assosa.
HelpAge International Ethiopia
Closes in 9 days
View Details
Ethio Telecom Notification of Bid Closing Date Extension and Addendum: National competitive bids are invited for the supply of pole accessories and cables, 11m impregnated wooden poles, 300 and 500 daN concrete poles, and various capacities of circuit breakers under RFQ Nos. 4287312, 4287313, 4287314, and 4287324.
Ethio Telecom
Closes in 13 days
View Details
Dugda Construction PLC invites interested and qualified bidders to submit sealed financial offers for the purchase of the following used construction materials and scrap, grouped into two lots
Dugda Construction
Closes in 2 days
View Details